top of page

​የሀገረ ስብከቱ ዋና ዓላማ
 

1/ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙትን አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መጠበቅና አገልግሎታቸውም የተሟላ እንዲሆን ማድረግ

2/ ከሐዋርያት ተያይዞ የመጣው ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ሥርዓት እንዳይፋለስ መጠበቅና ማስጠበቅ

3/ ጥንታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓተ አምልኮ በአግባቡ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ

4/ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በማፋጠንና መንፈሳዊ የአገልግሎት አድማስን በማስፋት፥ በሀገረ ስብከቱ አካባቢ የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን በእምነቱ እንዲጠነክርና በቁጥርም እንዲበዛ ማድረግ

5/ ወጣቶች በአግባቡ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ተረካቢዎች ይሆኑ ዘንድ፣ በትምህርተ ሃይማኖት ተመሥርተው ፥ በሥነ ምግባር ታንጸው የሚያድጉባቸውንና በየአጥቢያው ያሉ የሰንበት ት/ቤት ተቅዋማትን ማጠናከር

6/ ወጥ የሆነ ፕሮግራም በማዘጋጀት በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በስብከተ ወንጌል ማጠናከርና ማስፋፋት

7/ በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሰላም፥ በአንድነት፥ በመተሳሰብና በመረዳዳት በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲጸኑ ማስተማርና ማበረታታት

8/የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 2 በደነገገው መሠረት የወጡ እና ወደፊትም ተሻሽለው የሚወጡ ደንቦችን ማክበርና ማስከበር

abune_edited_edited.png

ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ

በጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ አሠረ ሐዋርያትን በመከተል የቤተ ክርስቲያን የሥልጣን ምንጭ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ሕይወትና ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ውሳኔ ሰጪ ሉአላዊ አካል እንደመሆኑ መጠን፣ «በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ባለው መሰረት በአግባቡ የመጠበቅና ለመንጋውም የመጠንቀቅ ከፍተኛ ኃላፊነትና አደራ አለበት። የሐዋ 20፥28

ይህ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ በተወሠነው ውሣኔ መሠረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ካሊፎርኒያ፤ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ተብሎ ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ተሠይሟል።

ሀገረ ስብከቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ኃይማኖት ትእዛዝና በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መሠረት ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩት የተመደቡ ሲሆን በስሩ 20 አብያተ ክርስቲያናት ያሉት ሀገረ ስብከት ነው።  

ስለ ሀገረ ስብከቱ

የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት 

የሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አድባራት እና ገዳማት

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ምደባ ደብዳቤ 

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሊቀ ጵጵስና ማዕረግ  ደብዳቤ 

Abba theo.jpg
bottom of page