top of page

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ታሪካዊና ሀገራዊ በመሆኗ አብያተ ክርስቲያናትን በማስፋፋት ለአማንያን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዓለም ዳርቻ እንዲዳረስ ፣ ቀኖናዊ የአበው ስርዓት እና ዶግማዊ ሕግ እንዲጠበቅ እንዲሁም ሀገራዊ ባህል በዓለም ዳርቻ እንዲደርስ ሐዋርያዊ ተልዕኮ በመወጣት ላይ ትገኛለች። የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ይህንኑ የቤተ ክርስቲያኗን ተልዕኮ ለመፈጸም እና ለማስፈጸም በቅዱስ ሲኖዶስ የ 2011 ዓ/ም ምልዓተ ጉባዔ ውሣኔ በብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳስ (ዶ/ር) ሀገረ ስብከቱ እንዲመራ ከተወሠነበት ጊዜ አንስቶ በአዲስ መልክ የተቋቋመ ሀገረ ስብከት ነው።

Mural decorations

የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ

 

ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር 

መንበረ ጵጵስና ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ወቅድስት አርሴማ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አንድነት ገዳም ሳን ሚጉዬል ካሊፎርኒያ 

የሐገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ

 

መልአከ ስብሃት ቆሞስ አባ ኃይለ ኢየሱስ ገሰሰ 

ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል

የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላስ ቬጋስ ኔቫዳ

የሐገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ

 

መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ተገኑ ወርቅነህ

መካነ ራማ ቅ/ገብርኤል

የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ

የሐገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ

ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ቡሩክ አልዩ 

ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል

የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላስ ቬጋስ ኔቫዳ

የሀገረ ስብከቱ ምሥረታ

የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ውሣኔ መሠረት ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም በብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር እንዲመራ ተወሠነ። ሀገረ ስብከቱን ለማደራጀት ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ስቴት የአጥቢያ ካህናትን ስብሰባ በመጥራት ኅዳር 29 ቀን 2011 ዓ/ም  ለሀገረ ስብከቱ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ አደረጃጀት ስፈላጊነት ላይ በመምከር እና ውሣኔ በማሳለፍ ሀገረ ስብከቱ ሊቋቋም ችሏል።

bottom of page